Your cart is currently empty!
የጨረታ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Aug 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ማስታወቂያ
ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ያቅራቢ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም የቫት የምዝገባ ሰርተፍኬት ከሚጫረታቸው ሰነዶች ጋር አባሪ መሆን ይኖርበታል፡፡ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300 ብር (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ቢሮ 2ኛ ፎቅ ላይ ፋይናንስ ፅ/ቤት በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 0.5% የጨረታ ማስከበሪያ ለፋይናንስ ፅ/ቤት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
2. የጨረታው ሰነድ ሲገባ ናሙና አብሮ መቅረብ አለበት ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡበት ሰነድ ዋናውና ፎቶ ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው፡፡
3. ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ከመስሪያ ቤታችን ጋር ውል ተዋውሎ የውል ማስከበሪያ ዋጋውን 10% ዋጋ ማስያዝ ይኖርበታል በተጨማሪ የአሸናፊውን እቃ በ10 ቀናት ውስጥ ማቅረብ ግዴታ አለበት ይህ ባይሆን ግን ለጨረታው የተያዘውን ሲፒኦ ዋጋ በቀጥታ ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
4. ጨረታው በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት ይዘጋል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
6. በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ አካላት በሀገር ውስጥ ምርት ላይ ብቻ መወዳደር ከፈለጉ ህጋዊ ማስረጃ ሲያቀርቡ ሰነድ ወስደው መወዳደር ይችላሉ፡፡
7. በጨረታው ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
8. ጽ/ቤቱ ከውል በፊት 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ ከውል በኋላ 25% የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. አንዱ በአንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
10. አሸናፊው ያሸነፈባቸውን ንብረቶች የወረዳው ንብረት ክፍል ድረስ አምጥተው ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
11. ተጫራቾች የአንዱ ነጠላ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጠቀስ አለበት ያልተጠቀሰ ከሆነ ቫት (እንዳካተተ) ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
12. እያንዳንዱ ተጫራች ለሚያስገባው ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
አድራሻ፡– ከፓስተር ወረድ ብሎ ወደ ጨው በረንዳ በሚወስደው መንገድ ፈለገ መለስ ጤና 400 ሜትር
ርቀት ላይ ወረዳ 6 አስተዳደር ገቢ ውስጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 011 273 5885 ወይም 011 277-4800
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር
ፋይናንስ ጽ/ቤት